1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሰዳጆች ዕጣ ፈንታ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2010

ስደት ካሰቡበት ለመድረስ ያለሙ በርካቶችን ከየሀገራቸው ስቦ በቤልጂግ መዲና ብራስልስ ከአንድ ስፍራ አድርሷቸዋል። ከእነዚህ መካከል ኢትዮጵያውያንም ይገኛሉ። አውሮጳ ስደተኞች ውቅያኖስን ተሻግረው እንዳይመጡ ጥረቷን ብታጠናክርም ተስፈኞቹ ተሰዳጆች ግን እዚህ ደርሰው፤ እንደገና ልባቸው ካሰበበት ዳግም ለመሰደድ ሲሞክሩ ይታያል።

https://p.dw.com/p/32Oy3
Brüssel Flüchtlinge in öffentlichem Park
ምስል DW/D. Sisay

የተሰዳጆች ዕጣ ፈንታ

እግሮቹ በቤልጂግ መዲና ብራስል ጎዳናዎች ላይ ሲመላለሱ አይታክታቸውም፤ አንዳች ግብ አላቸውና። ልቡ ግን በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ኢትዮጵያ ከእናታቸው ጋር የሚገኙት ሁለት ሕጻናት ልጆቹ ጋር ቀርቷል። ወጣቱ ኢትዮጵያዊ  ስደተኛ  ቀን እስኪሞላ ድረስ የሦስት እና የዓመት ከመንፈቅ ልጆቹ በዓይነ ኅሊናው እየተመላለሱ ናፍቆቱ ቢያስቸግረውም የዕንባ ዘለላውን ከማበስ ውጪ ግን ምንም ማድረግ አይችልም።  በእንዲህ ያለ የስደት አዙሪት ውስጥ ካሉት አንዱን ኢትዮጵያዊ ወጣት  እዛው ብራስልስ ውስጥ አነጋግሮት ዳግማዊ ሲሳይ ለዕለቱ አውሮጳ እና ጀርመን መሰናዶ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል። 

ዳግማዊ ሲሳይ

ሸዋዬ ለገሠ