1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የብር ዋጋ መቀነስ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 1 2010

የብር ዋጋ መቀነስ ላጭር ጊዜ እፎይታ መጥቀሙ አይቀርም።በረጅም ጊዜ ግን የሸቀጦች ዋጋ ንረትን እና የኑሮ ዉድነትን ያስከትላል

https://p.dw.com/p/2leYb
Geldscheine
ምስል DW/E. Bekele Tekle

(Beri.AA) Ethio.Birr Devaluation - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር ምንዛሪ ዋጋን መቀነሱ የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል አንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አስታወቁ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ ባለሙያ እንደሚሉት የብር ዋጋ መቀነስ ላጭር ጊዜ እፎይታ መጥቀሙ አይቀርም።በረጅም ጊዜ ግን የሸቀጦች ዋጋ ንረትን እና የኑሮ ዉድነትን ያስከትላል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንድ የብር የምንዛሪ ዋጋን በ15 ከመቶ ቀንሷል።