1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባኤ

ሰኞ፣ ነሐሴ 7 2010

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የመግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባኤ በያዝነው የነሐሴ ወር መጨረሻ አሊያም በመጪው ጳጉሜ ወር ውስጥ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/336Y4
AEUP
ምስል DW/G.Tedla HG

ጉባኤው በወሩ መጨረሻ ይካሄዳል ተብሏል

ጉባኤውን እያዘጋጁ ያሉት አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጉባኤው በሀገር ቤትም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ የሚሳተፉበት ነው ብለዋል። ለዚሁ ጉባኤ የግብዓት ማሳባሰቢያ ይሆን ዘንድ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 ዓ ም በሚደረገው ምክክርም ገዢው ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ፓርቲዎችም እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

ሂሩት መለሰ