1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጅግ የተገን ጠያቂዎች ቢሮ ውሳኔ

ዓርብ፣ ነሐሴ 11 2010

የቤልጅግ መንግስት አሁን ያለውን የተገን ጠያቂዎች ቢሮ በዚህ ወር መጨረሻ ሊዘጋ ነው። ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሮ ስራ እንደሚጀምር የገለፁት የቤልጅግ መንግስት ተገን ጠያቂዎችና ፍልሰተኞች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲዮ ፍራንከን ከቭላምስ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

https://p.dw.com/p/33KFz
Brüssel Inoffizielles Zeltlager für Flüchtlinge im Parc Maximilien
ምስል Reuters/Y. Herman

በብራስልሱ መናፈሻ በርካቶች ይኖራሉ

ብራስልስ ደቡብ ቢሯቸው ፊት ለፊት የሚገኘው ማክሲሚላን መናፈሻ "የህገ ወጥ ፍልሰተኞች" መናኸሪያ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ይህንን እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱ ሚኒስትሩ ቲዮ ፍራንከን ተናግረዋል። ወደ እንግሊዝ ለመግባት ከተለያዩ ቦታዎች የሚሰባሰቡት እነዚሁ ፍልሰተኞች መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ባይታወቅም እኚሁ ሚኒስትር ግን ወደ "ሀገራቸው በግድም ቢሆን እንመልሳቸዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል። በመጪው ጥቅምት 2018 ሀገር አቀፍ ምርጫ የምታካሒደው ቤልጅግ የፖለቲካ ፓርቲዎቿ የተገን ፈላጊዎችን ጉዳይ እንደ አንድ የምርጫ ቅስቀሳ መሳሪያም ይጠቀሙበታል። ውሎ አዳራቸው በእዚህ መናፈሻ ስፍራ ካደረጉ መካከል የኢትዮጵያውያኑን ሁኔታ ከዚህ ቀደም በሳምንታዊ መሰናዶ ያስደመጠን ዳግማዊ ሲሳይ ከብራስልስ ይህ ውሳኔ ይፋ ከሆነ በኋላ ያለውን እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ዳግማዊ ሲሳይ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ