1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ኢትዮጵያዉያኑ በሰላም እንዲመለሱ እየጣርን ነዉ» የጂዳ ቆንስላ

ዓርብ፣ ሰኔ 16 2009

የስዑዲ አረብያ መንግሥት በሃገሪቱ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሚኖሩ የዉጭ ሃገር ዜጎች  እንዲወጡ ያስቀመጠዉ ቀነ-ገደብ  ሳያራዝም አይቀርም የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነዉ።ይሁንና  በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ወሬዉን ከሕጋዊ ምንጭ ማረጋገጥ አልተቻለም።

https://p.dw.com/p/2fILz
Saudi Arabien Dschidda
ምስል Getty Images/AFP/K. Saad

M M T/ Exk.Inter.mit Botschafter Wubhet Demissie in Jeddah über Saudi Rückkehrer - MP3-Stereo

በስዑድ አረብያ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሚኖሩ አንዳድ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ የመንን ወደ መሳሰሉ ሃገራት ከመፍለስ ይልቅ ወደ ሃገራቸዉ ቢመለሱ እንደሚሻል ቆንስላዉ  ምክር ለግሶአል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያስቀመጠዉ  ቀነ ገደብ ፤ ሊራዘም ይችላል ነገ መግለጫ ይወጣል የሚለዉ ተናፋሽ ወሬን ማረጋገጥ አይቻልም ፤ በስዑዲ መንግሥት በኩልም የምሕረት አዋጁ እዚህ ጋር ይቆማል ተብሎ መግለጫ አልተሰጠም ሲሉ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ተናግረዋል።

ቆንፅላ ጽ/ቤቱ መመለስ ለሚሹ ኢትዮጵያዉያን ሰነድ ከመስጠት ባሻገር ትራንስፖርት እንዲያገኙ ሁሉ ጥረት እያደረገ መሆኑም ታዉቋል።

በስዑድ አረብያ ሕገ-ወጥ የተባሉት ኢትዮጵያዉያንን ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የባሕር መስመር የሚያቀርብ አካል ካለ እድሉን ሰጥተናል ሲሉም  አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ተናግረዋል።

መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመለሱ ዜጎች የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣል ። በዚህም ከስዑዲ አረብያ የሚፈናቀለዉ ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሩ ወደ ወገኑ ቢገባ እመክራለሁ ሲሉ አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ገልፀዋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ