1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተከሳሾቹ ጉዳይ በግልጽ ችሎት ይታያል፤

ረቡዕ፣ ጥቅምት 29 2010

ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ቱጃር መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት የሳዑዲ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከፍተኛ ባለሀብቶች ላይ የተከፈተው የሙስና ክስ ፈጣን እና ግልጽ በሆነ ችሎት እንደሚታይ የሳዑዲ ዓረቢያ ዋና አቃቤ ሕግ አስታወቁ ፡፡

https://p.dw.com/p/2nI8U
Saudi Arabien Vision 2030 PK Mohammed bin Salman
ምስል /Getty Images/AFP/F. Nureldine

ጉዳያቸዉ በግልጽ ችሎት ይታያል፤

አስራ አንድ ልዑላዊ ቤተሰቦች ፣ ከሰላሳ በላይ ከፍተኛ ባለ ሀብቶች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናትን አስጠርጥሮ ለእስር የዳረገው ዘመቻ ፤ ሙስናን ከስር መሰረቱ የመንቀል የመጀመሪያው ምዕራፍ መሆኑ ተገልጧል ፡፡ በቀጣይ ምዕራፍም ከ አንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ባለስልጣናት እና ባለ ሀብቶች ጉዳያቸው ይታያል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የንጉስ ሰልማን እና የአልጋ ወራሹን ድርጊት አወድሰዋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ሼክ መሀመድ አላሙዲን በቢሊዮን ዶላሮች በሚገመቱ ሁለት ጉዳዮች ስማቸው መጠቀሱን የክሱን ሂደት የሚከታተሉ በሪያድ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ለዶቸ ቨለ ገልጸዋል። ። 

ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋኅ መሐመድ