1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመን መንግሥት ተቀናቃኝ ኃይሎች መጋጨት

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 1 2009

ባለፈው ሳምንት በተከሰተው ግጭት አንድ የአብደላ ሳልህ ከፍተኛ መኮንን እና አማጽያን ተገድለዋል። ይሁንና፣ ሳልህ በሰጡት መግለጫ በመካከላቸው ምንም ዓይነት ቀውስም ሆነ ግጭት እንደሌለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2jSnz
Jemens Ex-Präsident Ali Abdullah Saleh
ምስል Getty Images/AFP/M. Huwais

የየመን መንግሥት ተቀናቃኝ ኃይሎች ግጭት

ግንባር ፈጥረው የየመንን መንግሥት ሲወጉ የቆዩት የቀድሞ የየመን ፕሬዝዳንት የአሊ አብዱላ ሳልህ ታማኞች እና የሁቲ አማጽያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደ ቀድሞአቸው አይደሉም። አንዳቸው ሌላኛቸውን በሙስና እና ከበስተጀርባ በማጥቃት ሲወቃቀሱ የከረሞት ሁለቱ ወገኖች መቃቃራቸው ይሰማል። ከዚያም አልፈው ባለፈው ሳምንት ተጋጭተው አንድ የሳህል ከፍተኛ መኮንን እና አማጽያን ተገድለዋል። ይሁን እና ሳልህ በሰጡት መግለጫ በመካከላቸው ምንም ዓይነት ቀውስም ሆነ ግጭት እንደሌለ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የመን ውስጥ በኮሌራ የተያዘው ሰው ቁጥር 612,703 መድረሱ ተነግሯል። ስለ ሳህል ኃይሎች እና ስለ ሁቱ አማጽያን ግጭት እንዲሁም ስለ የመኑ ኮሌራ የሰንአውን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖትን ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።


ግሩም ተክለ ሃይማኖት 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ