1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰመጉ ዘገባ

ዓርብ፣ ኅዳር 1 2010

በግጭቶች ወቅት በሚደርስ የሰዎች ህይወት ጥፋት እና በንብረት ውድመት ተጠያቂ በተባሉ በታች ደረጃ በሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ላይ ከዓመታት በኋላ ቅጣት ቢወሰንም ይህ ብቻውን በቂ እንዳይደለ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/2nPgC
Äthiopien - Human Rights Council (HRCO)
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

የሰመጉ ዘገባ

በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ለደረሱ የሰው ህይወት ጥፋትም ሆነ ለንብረት ውድመት ተጠያቂ በተባሉ በታች ደረጃ በሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ላይ ከዓመታት በኋላ ቅጣት መወሰን ብቻውን በቂ እንዳይደለ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ።በዚህ ሳምንት በሁለት አካባቢዎች የተፈጸሙ ብሔር ተኮር ያላቸው የመብት ጥሰቶች ላይ ያተኮረ ልዩ ዘገባ ያቀረበው የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቁምላቸው ዳኜ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሩ በአንዳንድ ሁኔታዎች የቅጣቱ ውሳኔ የጥፋቱን አቀነባባሪዎች አለማካተቱ ነው። እናም ይህ መፈተሽ እንዳለበት ሃላፊው አሳስበዋል። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ