ሕግ አስከባሪ ተቋማት ለሕግ ተገዢ መሆን አለባቸዉ።
ዓርብ፣ ሰኔ 22 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕግ አስከባሪ አካላት እና ተቋማት በአዲስ መልክ እንዲደራጁ የሰብአዊ መብት ጉባኤ ዛሬ ጠየቀ።የጉባኤዉ ባለሥልጣናት በሰጡት መገለጫ ሕግ አስከባሪ ተቋማት ለሕግ ተገዢ እና የዜጎችን መብት ጠባቂ ሆነዉ ሊደራጁ ይገባል።ጉባኤዉ እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ-ሽብር ሕግን፤ የበጎ አድራጎት እና የፕሬስ ሕጎችን መሻር ወይም ማሻሻል አለበት።እስካሁን ያልተፈቱ እስረኞች እንዲለቀቁ፤ የተለቀቁትም ወደ ቀድሞ ሥራቸዉ እና ኑሯቸዉ እንዲመለሱ መንግሥት እገዛ ያደርግላቸዉ ዘንድ የሠመጉ መሪዎች ጠይቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ