1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 26 2010

ሰማያዊ ፓርቲ ቤተ እምነቶች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ርቀው ሰላም እና ፍቅርን እንዲሰብኩም ጠይቋል። በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችንም መንግሥት በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሞክር ጥሪ አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/32VkA
Äthiopien, Addis Abeba: Blue Party Pressekonferenz
ምስል DW/G. Tedla

«የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፍቅር እና የመግባባት እርምጃዎች እንደግፋለን»ሰማያዊ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ ለማገዝ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች እና አንድ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረበ። የፓርቲው አመራር አባላት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እነዚህ ወገኖችም ሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ መጠበቅ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ቤተ እምነቶች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ርቀው ሰላም እና ፍቅርን እንዲሰብኩም ጠይቀዋል። በለውጡ ሂደት ትልቁን ሚና የሚጫወቱትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን እና ባልደረቦቻቸውን ያመሰገኑት የአመራር አባላቱ በአሁኑ ጊዜ መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሞክርም ጥሪ አስተላልፈዋል።  

 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ