1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ

ረቡዕ፣ ሰኔ 20 2010

የፓርቲው አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጋር በአንድ መድረክ ተገናኝቶ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ከመቀበል አንስቶ የሚያስፈልጋቸውን እገዛ በማድረግ እንደሚተባበርም ፓርቲው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/30O9H
Blue Party-Versammlung Äthiopien
ምስል DW/G. Tedla HG

ሰማያዊ ፓርቲ

ተቃዋሚው የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ጥሪ ከተደረገላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀ። የፓርቲው አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጋር በአንድ መድረክ ተገናኝቶ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ከመቀበል አንስቶ የሚያስፈልጋቸውን እገዛ በማድረግ እንደሚተባበርም ፓርቲው ገልጿል።  በዚሁ መግለጫው ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት አውግዞ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ