1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የር/ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዋሽንግተን አዲስ አበባ መግባት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 2010

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ያለፉት 26 ዓመታትን በስደት ከቆዩባት ዩኤስ አሜሪካ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።

https://p.dw.com/p/32Sda
Äthiopien Orthodoxe Kirche Patriarch
ምስል Prime Minister Office/Fitsum Arega

ከፍተኛው መንፈሣዊ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጋር በአንድነት ቦሌ ኢየር ማረፊያ በደረሱበት ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ስድስተኛ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ እና ከፍተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባላት እና ህብረትሰኑ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከሳቸው ጋር 19 ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች አብረዋቸው ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆን፣ ሁሉም በቅድስት ሥላሤ ካቴድራል በተዘጋጀው የፀሎት ስነ ስርዓት ላይ ተካፋዮች ሆነዋል።

 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ