1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የረሐብ አድማና ተቃውሞ በቂሊንጦ እስር ቤት 

ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2010

በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ ሰዎች  ከትላንት ጀምሮ የረሐብ አድማ ላይ መሆናቸው ተነገረ። እስረኞቹ፦ ግንቦት 7 እና ኦነግ  የአሸባሪነት ክስ እና ፍረጃ ሲነሳላቸው ፣በአሸባሪነት ተከሰው የነበሩ ግለሰቦችም ሲፈቱ የእኛን ጉዳይ የሚመለከት ጠፍቷል በሚል ምሬት የረሐብ አድማ መጀመራቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/31PzI
Symbolbild Justiz Richter Gericht Richterhammer
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

እስረኖቹ «እኛ አልተደመርንም ተቀነስን እንጂ» ብለዋል

በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ ሰዎች ከትላንት ጀምሮ የረሐብ አድማ ላይ መሆናቸው ተነገረ። እስረኞቹ፦ ግንቦት 7 እና ኦነግ የአሸባሪነት ክስ እና ፍረጃ ሲነሳላቸው ፣በአሸባሪነት ተከሰው የነበሩ ግለሰቦችም ሲፈቱ የእኛን ጉዳይ የሚመለከት ጠፍቷል በሚል ምሬት የረሐብ አድማ መጀመራቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ተናግረዋል።

ከታሳሪ ቤተሰቦች በተገኘ መረጃ መሰረት፦ ከረሐብ አድማው በኋላ «ብሉ አትብሉ» በሚል በተነሳው ተቃውሞ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እንደተኮሰ እና ወደ ሦስት የሚጠጉ እስረኞች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል ። በሽብር ለተከሰሱ ስድስት መቶ እስረኞች ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የሰጡ እና በአሁኑ ወቅት ወደ 80 ለሚጠጉ በአሸባሪነት ለተከሰሱ እስረኞች ጥብቅና የቆሙት ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ የደንበኞቻቸው ቤተሰቦች የነገሯቸውን ለዶቼቬለ አስረድተዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ