1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥራ እድል ለሳዑዲ ተመላሾች

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ሰኔ 8 2009

በሳዑዲ አራብያ ያለ ህጋዊ ፍቃድ የሚኖሩ ወደ 400,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ ይገመታል። በሳዑዲ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሚኖሩ ዜጎች ሃገሪቱን ጥለዉ እንዲወጡ የተሰጣቸዉ የሦስት ወር ቀነ ገደብ ሊያልቅ ደግሞ ሁለት ሳምንት ገደማ ቀርቶታል።

https://p.dw.com/p/2elXC
Saudi Arabien Arbeiter kehren nach Äthiopien zurück
ምስል DW/S. Shiberu

MMT Job Promise for Saudi Returnee - MP3-Stereo

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ብሔራዊ አስመላሽ ኮሚቴ ግብረሃይል ወደ ሳዑዲ በሚገኘዉ ኤምባሲና፣ በቆንሱላ ጽሕፈት ቤት ሰባት ማዕከላት ተቋቁሞ ዜጎቹ እዛ መጥተዉ እንሲመዘገቡ እያደረጉ እንደሚገኙ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የጉዞ ሰነድን  ወስደዋል የተባሉት ዜጎች ከ50,000 በላይ ቢሆኑም ቀሪዎቹ አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ላለመመለስ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶችን ማቅረባቸዉ ነዉ የሚነገረዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ ሲመለሱ የሥራ እድል እንደሚፈጥርላቸዉ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

ዜጎቹን ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ አያር መንገድ የትኬት ዋጋን ቀደም ሲል 180,000 ሪያል ያወጣ የነበረዉ አሁን በመቀነስ 90,000 ሪያል እንዳደረገና 21 እቃዎችን በቀረጥ ነፃ እንድያስገቡ ማደረጉን አቶ ግርማ ተናግረዋል።

በሳዑዲም ሆነ በአገር ዉስጥ ያሉ ይህን የመንግስት የሥራ ፈጠራ እቅድ በጥርጣሬ የሚመለከቱት አልጠፉም። የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ፈጠራ እቅድ እንዴት ትመለከቱታለችሁ ብለን አስተያየት ጠይቀንም ነበር።

Illegale aus Äthiopien in Saudi-Arabien
ምስል DW/Sileshi Sibiru

የአባት ስማቸዉን ያልጠቀሱት ከሳዑዲ መመለሳቸዉን የተናገሩት አቶ ታጠቅ መንግሥስት በፖለቲካ አቋማቸዉ በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲደራጁ ሲጠየቁ እንዳልተቀበሉት በዶይቼ ቬሌ ዋትሳፕ ላይ የድምፅ መልክት ልከዉልናል።

አገር ዉስጥ ላሉትም ዜጎች መንግሥት የሥራ እድል እፈጥራለሁ የሚለዉ «ወሬ» ብቻ ነዉ፣ አሁን ለሳዑዲ ተመላሾች እየተገባ ያለዉ ቃልም ተመሳሳይ ነዉ የሚል አስተያየት አብዛኞች ተከታታዮቻችን ልከዉልናል።ወደ አምስት ዓመት ሳዑዲ አራብያ መቀመጣቸዉን የተናገሩት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁን ሌላዉ አስተያየት ሰጭ መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ የ10 ቢሊዮን ብር የሥራ እድል ፈጠራ እቅድ የት ገባ ሲሉ ጠይቀዋል።

በ2006 ዓ.ም የሳዑዲ መንግስት በሃገሪቱ የነበሩና ሕገወጥ ያላቸዉን ወደ 250,000 የሚሆኑ የተለያዩ አገር ዜጎች ከአገሩ ማስወጣቱ ይታወሳል። ከዚህም ዉስጥ ከ 160,000 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዉያን ነበሩ።

መርጋ ዮናስ

አዘብ ታደሰ