1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም» ራይላ ኦዲንጋ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 21 2010

የኬንያ የምርጫ እና ድንበር አካላይ ኮሚሽን ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምጽ አግኝተው መመረጣቸውን ትናንት ማውጁን ተከትሎ የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ከሰዐት በኋላ ስለ ቀጣይ የፖለቲካ ትግል አቅጣጫቸው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2mpNM
Kenia Wahlwiederholung Raila Odinga
ምስል picture-alliance/dpa/D. Bandic

ራይላ ኦዲንጋ መጠነ ሰፊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጥሪ አስተላለፉ

የኬንያ የምርጫ እና ድንበር አካላይ ኮሚሽን ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምጽ አግኝተው መመረጣቸውን ትናንት ማውጁን ተከትሎ ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ከሰዐት በኋላ ስለ ቀጣይ የፖለቲካ ትግል አቅጣጫቸው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ኦዲንጋ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በቅርቡ ሰፊ መሠረት ያለው እና የሃይማኖት ተቋማትን፣ ሲቪል ማኅበራትን፣ ፖሊከኞችን እና ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ሕዝባዊ ሸንጎ እንዲሁም የዕለት ተለት ጉዳዮችን የሚከታተል ግብረ-ኃይል ይቋቋማል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከብሔራዊ ልዕለ-ጥምረት (National Super Alliance) ወደ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሸጋገረው ፓርቲያቸው ሰላማዊ የአደባባይ ተቃውሞን እና የኢኮኖሚ ማዕቀብን ያጣመረ የትግል ስልት እንደሚከተል የገለጹት ኦዲንጋ አዲሱ ግብረ ኃይልም ሕገ መንግስታዊ ማሻሻያዎችን ጭምር እንደሚያቀርብ ነው በመግለጫቸው ያስታወቁት፡፡ አያይዘውም ገለልተኛው የምርጫ ኮሚሽን የሐሙሱ ምርጫ ሂደት ዋነኛ ባለቤት መሆን እንዳልቻለ የጠቆሙ ሲሆን «ይሄ ምርጫ ተቀባይነት ካገኘ በኬንያ የምርጫ ሳጥን የሥልጣን መወጣጫ መሆኑ ያከትማል» ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የኦዲንጋ ቀጣይ ርምጃዎች ሀገሪቱ የገጠማትን ፖለቲካዊ ቀውስ እንዳያባብሰው ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

ቻላቸው ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ