1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙስና ተጠርጣሪዎች የችሎት ውሎ

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 26 ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ዛሬ ፈቅዷል። በእነ ብርጋዲየር ጄነራል ጠና ቁርንዲ መዝገብ ያሉ የእነዚህንን ተጠርጣሪዎች ቀጣይ ሂደት ለመመልከትም ለታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

https://p.dw.com/p/39AOk
Symbolbild Deutschland Justiz
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

የሙስና ተጠርጣሪዎች የችሎት ውሎ

በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦችም እንዳለፉት ቀናት ሁሉ ዛሬም ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። የጊዜ ቀጠሮ መዝገባቸውን እየተመለከተ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ፖሊስ በጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ላይ ዛሬ ውሳኔ ሰጥቷል። 

ችሎቱ በትላንትናው ውሎው የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቡትን መቃወሚያ ያደመጠ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ለመቃወሚያው ፖሊስ የሰጠውን ምላሽ ሰምቷል። የዛሬውን የችሎት ውሎ ከተከታተለው ዘጋቢያችን ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ። 

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር

ተስፋለም ወልደየስ 

ኂሩት መለሰ