1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠበቆቻቸው ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል

ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

ከ7-22 አመታት እስር ተበይኖባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት አሕመዲን ጀበል፣ ካሊድ ኢብራሒም፣ አሕመድ ሙስጠፋ እና መሐመድ አባተ በሥር ፍርድ ቤት የተወሰነባቸው ቅጣት የሕግ ስሕተት አለበት ሲሉ ይግባኝ ጠየቁ። ጠበቆቻቸው "ደንበኞቻችን ይግባኝ የማቅረብ ፍላጎታቸውን ከገለጹ ከሶስት አመታት በላይ ሆኗቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2sHr6
Äthiopischer "Muslim Arbitration" Komitee Mitglied
ምስል A. Ahmed

የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይግባኝ

አራት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በሥር ፍርድ ቤት የተወሰነባቸው ቅጣት የሕግ ስሕተት አለበት በማለት ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለዋል። በጠበቆቻቸው በኩል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን ያቀረቡት አሕመዲን ጀበል፣ ካሊድ ኢብራሒም፣ አሕመድ ሙስጠፋ እና መሐመድ አባተ ናቸው። ጠበቃ መሐመድ አብደላ ከችሎቱ በኋላ እንደተናገሩት "ደንበኞቻችን ይግባኝ የማቅረብ ፍላጎታቸውን ከገለጹ ከሶስት አመታት በላይ ሆኗቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ጠበቃ መሐመድ ደንበኞቻቸው የተፋጠነ ፍትኅ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። አሕመዲን ጀበል፣ ካሊድ ኢብራሒም፣ አሕመድ ሙስጠፋ እና መሐመድ አባተ ከ7-22 አመታት ተፈርዶባቸው ማረሚያ ቤት ይገኛሉ። ጉዳዩን ያዳመጠው ፍርድ ቤት ለመጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠበቃ አዲስ አሕመድ እና ጠበቃ መሐመድ አብደላ ግን ደንበኞቻቸው ከዚያ በፊት ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ተስፋ አሳድረዋል። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ