የመድረክ መግለጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ
ሰኞ፣ የካቲት 19 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ አውጥቷል። አስራ ሶስት ነጥቦችን ከያዘው የመድረክ መግለጫ በሀገሪቱ ይታያሉ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል። ከእነዚህም ውስጥ ህዝብ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ ሲንቀሳቀስ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ እንደሚወሰድበት የሚጠቅሰው ይገኝበታል።
በኢትዮጵያ ፍትሃዊ የሆነ ስርዓት አለመዘርጋቱን፣ በሀገሪቱ የፍትህ መዛባት እና ሙስና መንገሱን ይጠቅሳል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ስለ መግለጫው ይዘት የመድረክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የውጭ ግንኙነት ሃላፊን ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን አነጋግሯል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ