1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመራሒተ መንግሥቷ እጣ ፈንታ

ማክሰኞ፣ መስከረም 22 2011

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሰሙኑን በጀርመን ፖለቲካ መድረክ ቀላል ቀናትን አላሳለፉም። ባለፉት ሳምንታት ፓርቲያቸዉ ሰራቸዉ ስለተባለዉ ስህተት እንዲያምኑ መገደዳቸዉ፤ ፓርቲያቸው ባካሄደው የምክር ቤት አንጃ መሪ ምርጫ ላይ እሳቸው የሚደግፉትን እጩ ማስመረጥ አለመቻላቸው በሥልጣን የመቆየታቸዉን ነገር አዳጋች ሳያደርገው እንዳልቀረ ተገምቷል።

https://p.dw.com/p/35rXG
Karikatur von Sergey Elkin Insa-Umfrage

የሜርክል የመጨረሻዉ መጀመርያ


የጀርመንዋ መርሃቲ መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት በተመረጡ በስድስት ወራቸዉ የጣምራዉን መንግሥት ሲመሰርቱ ጀርመንን ለአራት ዓመት በድጋሚ በመራሒተ-መንግሥትነት    ያለችግር ያስተዳድራሉ ተብሎ ተገምቶ  ነበር። መራሒተ- መንግሥትዋ ጀርመንን ብቻ ሳይሆን በያዝነዉ በ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን አዉሮጳን መርተዉ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚያደርሱም ተጠብቀው  ነበር። ግን ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ፓርቲያቸው ባካሄደው ምርጫ  አንጌላ ሜርክል እንደገና በፌዴራዊው ምክር ቤት የክርስትያን ዲሞክራቱ ሕብረት እና «የክርስትያን ሶሻል ሕብረት አንጃ መሪ ሆነው ድጋሚ እንዲመረጡ የደገፏቸው የቀኝ እጃቸዉ የሚባሉት ሚስተር ፎልከር ካውደር መሸነፋቸው  የመራሂተ መንግሥትዋን  በስልጣን  የመቆየታቸዉን ነገር  አጠራጣሪ አድርጎታል። መራሒተ መንግሥትዋ  እንደራሴዎቹ ፊት ቀርበዉ «ካለእናንተ ድጋፍ ብቻዬን ምንም ማድረግ የማልችል ነኝ » በማለት ፣  ፈልከር ካዉደርም እንደገና እንዲመርጡ ተማጽነው ነበር፣ ግን ተማጽኗቸው ሳሚ ሳያገኝ ቀርቶ፣ ላለፉት 13 ዓመታት የምክር ቤት አንጃ መሪ ሆነው ያገለገሉት እና የፓርቲ አባላትን ድጋፍ ያጡት ካውደር በምክትላቸው ራልፍ ብሪንክሀውስ ተተክተዋል። ይህም በመራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የስልጣን ዘመን ስጋት እንዲያጠላ አድርጓል።  ሙሉ ቅንብር የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 


ይልማ ኃይለሚካኤል 
አዜብ ታደሰ