1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ግድቡ በ2015 ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2011

ቅሬታ እና ፀጥታ።የግብፆች ቅሬታ ሁነኛ መልስ አላገኘም።ግድቡ የሚገነባበት የበኒ-ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ፀጥታም ባለፉት አምስት ስድት ወራት እንደታወከ ነዉ።ከድንበር ማዶ የሚገኘዉ የሱዳን ግዛት ሠላምም አስተማማኝ አይደለም።አቶ ፈቂሕመድ እንደሚሉት ለቅሬታዉ አብነቱ ከግብፅ ጋር ግልፅ ድርድር ማድረግ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3B0Ay
Ägypten Äthiopien Damm am Nil
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

GRD-to be oprational by 2022 (Für 040119) - MP3-Stereo

 

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታሠራዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ታሕሳስ 2013 ኤሌክትሪክ ማምረት እንደሚጀምር የሐገሪቱ የዉኃ፣የመስኖ እና ኃይል ሚንስትር አስታወቁ።ሚንስትር ስለሺ በቀለ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደነገሩት ግድቡ በ2015 ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ አገልግሎት ይሰጣል።«የሕዳሴ ግድብ» ተብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ግንባታዉ ሲጀመር ይጠናቀቃል የተባለዉ በ2009 ነበር።እስካሁን ለመዘገይቱ የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ።ኢትዮጵያዊዉ የዉኃ እና መስኖ ባለሙያ አቶ ፈቂአሕመድ ነጋሽ  እንደሚሉት ያሁኑ ዕቅድ በቅጡ የተጠና፣ ካለፈዉም ስሕተት ትምሕርት የተወሰደበት እና አሳማኝ ይመስላል።አቶ ፈቂአሕመድ ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

 

ግድቡ-ከአፍሪቃ አንደኛ ነዉ-ከተጠናቀቀ።6000 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ያመርታል።የሚፈጀዉም ገንዘብ እንደ ኢትዮጵያ ላለች ደሐ ሐገር ቀላል አይደለም።ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ።በዚያ ላይ እስካሁን እንደሰማነዉ ሜቴክን የመሳሰሉ ኩባንዮች እና ኃላፊዎቹ የቦጨቁና የሚቦጭቁት ገንዘብ ከብዛቱ ሥራዉን ማወኩ ፈተና ነዉ-የሆነዉ።
ኢትዮጵያዊዉ ከዕለት ጉርሱ ቀንሶ ያዋጣዉ ገንዘብ ለጥጋበኞች «ግሳት» መዋሉ ለብዙዎች ሐዘን፣ቁጭት፣ ለሁሉም አስተዛዛቢ ነዉ።ትናንት የተነገረዉ ካለፈዉ ለመለየቱም ማረጋገጪያ የለም።የናይል ትብብር፣ የምሥራቅ ናይል አሐጉራዊ ፅሕፈት ቤት ሥራ-አስኪያጅ ፈቂአሕመድ ነጋሽ እንደሚሉት ግን ያሁኑ ዕቅድ ካለፈዉ በብዙ መንገድ ይለያል።አሁንም ግን ገንዘብ እና ቅንጅት ወሳኝ ናቸዉ።
                                
የኢትዮጵያ መንግስት ለተለያዩ የዉጪ ኩባንዮች አዳዲስ ኮንትራቶች እየሰጠ ነዉ።አዳዲሶቹ ኩባንዮች እርስበርስ እና ከነባሮቹ ጋር ያለና የሚኖራቸዉ ቅንጅት አቶ ፈቂ አሕመድ እንደሚሉት ለዕቅዱ ስኬት፣ ለአጠቃላይ ግንባታዉም ዉጤት ወሳኝ ነዉ።
                                        
ቅሬታ እና ፀጥታ።የግብፆች ቅሬታ ሁነኛ መልስ አላገኘም።ግድቡ የሚገነባበት የበኒ-ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ፀጥታም ባለፉት አምስት ስድት ወራት እንደታወከ ነዉ።ከድንበር ማዶ የሚገኘዉ የሱዳን ግዛት ሠላምም አስተማማኝ አይደለም።አቶ ፈቂሕመድ እንደሚሉት ለቅሬታዉ አብነቱ ከግብፅ ጋር ግልፅ ድርድር ማድረግ ነዉ።
                                        
የፀጥታዉ መታወክ ግን አቶ ፈቂአሕመድን ብዙ አያሰጋም።ይሁንና ግድቡ የሕዝብ መሆኑን ሕዝብ እንዲያዉቀዉ፣ ከጥቅሙም እንዲጋራ ማድረግ አስፈላጊ-ነዉ ባለሙያዉ እንደመከሩት።                                  
መጀመሪያ «ፕሮጀክት X»፣ ኋላ «ሚሊኒየም»፣ ደግሞ በኋላ «ታላቁ ሕዳሴ» የተባለዉ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለዉ፣መጋቢት 2003 ነበር።

Äthiopien Grand Renaissance Staudamm
ምስል Reuters/T. Negeri

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ