1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላፕሴት ፕሮጀክት እና የኬንያ ስጋት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2010

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቅርቡ ሰላም ስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እና በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃሉ LAPSSET ተብሎ የሚታወቀው የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ወደብ ልማት ፕሮጄክት አደጋ እንደተጋረጠበት አንድ የኬንያ ጋዜጣ ዘገበ፡፡

https://p.dw.com/p/324ke
Kenia Lamu Hafenprojekt Kenias Präsident Kibaki und Äthiopiens Premier Zenawi
ምስል Reuters

የላፕሴት ፕሬጀክት በ2012 የተፈረመ ነው

ዘ ስታንዳርድ የተሰኘው የሀገሪቱ ዕለታዊ ጋዜጣ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ አሰብ ወደብ ማዞሯ ላፕሴት ፕሮጄክትን እና ኬንያ ገና እየገነባችው ያለውን በሕንድ ውቂያኖስ ዳርቻ የሚገኘውን ላሙ ወደብን ዋጋ ቢስ ያደርጋቸዋል፡፡ ጋዜጣው ባለሙያዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ስምምነት ኬንያ ላሙ ወደብን የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የገቢ እና ወጭ ንግድ ማዕከል ለማድረግ እና የሰሜናዊ ግዛቶቿን ለማልማት የያዘችውን መጠነ ሰፊ ዕቅድ ያኮላሸዋል የሚል ስር የሰደደ ስጋት አለ፡፡ ከናይሮቢ ቻላቸው ታደሰ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

ቻላቸው ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ