የላስ ቬጋስ ጥቃት
ሰኞ፣ መስከረም 22 2010ማስታወቂያ
ማንዳላይ ቤይ ከተባለው ሆቴል ላይ ሆኖ የኅገረሰብ ሙዚቃ ዝግጅት ታዳሚያን ላይ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ መገደሉን ፖሊስ አረጋግጧል። ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱ የተፈጸመው ከበርካታ ወራት በፊት ኃይማኖቱን ወደ እስልምና በቀየረ ወታደር የተፈጸመ ነው ብሏል። ስለጥቃቱ የአሜሪካው ወኪላችን መክብብ ሸዋን ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ።
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ