የሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ
ረቡዕ፣ መስከረም 10 2010ማስታወቂያ
ባለፈው ዓመት በቢሾፍቱው የኢሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠያቂ ነው ተባለ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ስለ እሬቻው አደጋ ባወጣው ዘገባ መንግሥት ከቀደሙት ዓመታት በተለየ አምና በዓሉ በተከበረበት ቦታ ላይ በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ማሰማራቱን አስታውሶ የበዓሉን ሂደት ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ የአሳዛኙ አደጋ መንስኤ ሆኗል ብሏል። መንግሥት በዘንድሮዉ በዓል ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ አቅርቧል። ስለ ዘገባው የድርጅቱን የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳዮች አጥኚ ፌሊክስ ሆርንን ያነጋገረው የቶሮንቶው ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
አክመል ነጋሽ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ