1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀረሪ ክልላዊ መስተዳድር ዉጥረት

ማክሰኞ፣ ጥር 7 2011

በሀረሪ ክልላዊ መስተዳድር ነገሮች ዕለት ተዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየሆኑ የሄዱ ይመስላሉ ፡፡ የህግ የበላይነት ማስከበር ፈተና እንደሆነበት የሚነገረው የክልሉ ፖሊስም ሆነ መስተዳድሩ በየጊዜው የሚነሱ የህግ የበላይነት አለመከበር ጥያቄዎች መፍትሄ እየሰጠ ላለመሆኑ ማሳያዎች እየበዙ መተዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/3Bbi2
Äthiopien Gidir Magala Markt in der Altstadt von Harar
ምስል picture-alliance/dpa/J. Sweeney

በሀረሪ ክልላዊ መስተዳድር ነገሮች ዕለት ተዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየሆኑ የሄዱ ይመስላሉ ፡፡ የህግ የበላይነት ማስከበር ፈተና እንደሆነበት የሚነገረው የክልሉ ፖሊስም ሆነ መስተዳድሩ በየጊዜው የሚነሱ የህግ የበላይነት አለመከበር ጥያቄዎች መፍትሄ እየሰጠ ላለመሆኑ ማሳያዎች እየበዙ መተዋል ፡፡ በዛሬው ዕለት በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት  ስራቸውን አቁመዋል ፡፡ በዛሬው ዕለት በክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በሰላም ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ተሰባስበው የነበሩ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ስብሰባው ባልታወቀ ምክንያት መበተኑን ተከትሎ ስራቸውን አቁመዋል፡፡ በፕሬዝዳንቱ ፅ/ቤት ሰራተኞች ለስብሰባ መገኘታቸውን በሚመለከት በደረሰኝ መረጃ ወደዚያው ሄጄ በርካታ ሰራተኞች ተሰባስበው ተመልክቻለሁ ፤ይሁን እንጂ ስብሰባው ባልታወቀ ምክንያት ሳይካሄድ ተበትኗል ፡፡ውጥረት የነገሰ ድባብ ባየሁበት የፕሪዝዳንቱ ፅ/ቤት ግቢ ሊካሄድ የታቀደው ስብሰባ የተቋረጠበትን ምክንያት በሚመለከት ለመሰብሰብ ከመጣው ሰራተኛ መረጃ ማግኘት ባልችልም ከሰዓት በኃላ አንድ የክልሉን የስራ ሀላፊ በስልክ አነጋግረን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው የመንግስት ባለስልጣን የትናንቱ ጥቃት የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ እና የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት አቶ ነቢል መሀዲ ላይ ያነጣጠረ መሆኑንና ምክንያት ያሉትን ገልፀዋል ፡፡በክልሉ የመንግስት ተቋማት የተቋረጠው ስራ መቼ እንደሚጀመር ላቀረብነው ጥያቄ ሀላፊው ሲመልሱ ፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር ረምዚ ሱልጣን ትናንት የተፈፈፀመው ጥቃት ተከትሎ ፖሊስ እስካሁን ምንም ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ባያውልም ባካሄደው ምርመራ ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን የመለየት ስራ መሰራቱን አብራርተዋል ፡፡ፖሊስ ትናንት የተፈፀመውን ድርጊት ምርመራ ከማካሄድ ጎን  ለጎን ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ እየሰራ መሆኑን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡  ቦታዉ ላይ የሚገኘዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል። 

 


መሳይ ተክሉ
አዜብ ታደሰ 

ተስፋለም ወልደየስ