ዛሬ የተጠናቀቀዉ የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ
ዓርብ፣ ጥቅምት 10 2010ማስታወቂያ
ተሰብሳቢዎቹ በዉይይታቸዉ ወቅት የኅብረቱን የዉጭ ድንበር የመቆጣጠሩ ርምጃ ወደአዉሮጳ ዘልቀዉ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር መቀነስ ማስቻሉን አመልክተዋል። ከዚህም ሌላ በብሪታንያ ከአባልነት የመዉጣት ሂደት ላይ የተነጋገሩ ሲሆን፤ ከኢራን ጋር የተደረሰዉ የአቶም መርሃግብር ስምምነትን አፅንተዉ እንዲሚቀጥሉም አዉስተዋል። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ