1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለኖቤል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 2 2010

የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኸርማን ኮሕን እንደሚሉት ዶክተር ዐብይ ለጀመሩት የአንድነት እና የዴሞክራሲ መርሕ ኖቦል ቢሸለሙ ይደግፋሉ

https://p.dw.com/p/32pjH
Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል picture-alliance/AA

(Beri.Frankfurt) PM Abiy Nobel Nomination - MP3-Stereo

 የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለታላቁ የዓለም የሠላም ሽልማት ለኖቤል እንዲታጩ ሁለት የዉጪ ፖለቲከኞች ድጋፍ መስጠታቸዉን አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን እንዲይዝ ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዋል የሚባሉት የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኸርማን ኮሕን እንደሚሉት ዶክተር አብይ ለጀመሩት የአንድነት እና የዴሞክራሲ መርሕ ኖቦል ቢሸለሙ ይደግፋሉ። የስዊድን የምክር ቤት እንደራሴ አንድረሽ ኦስተንበርግ በበኩላቸዉ ዶክተር ዐብይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢዉም ሠላም የሚጠቅም እርምጃ እየወሰዱ ነዉ። የፍራንክፍረቱ ወኪላችን እንዳልካቸዉ ፍቃደ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

እንዳልካቸዉ ፈቃደ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ