1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ግንኙነት፤ የኢህአዴግ ዉሳኔና ህወሓት

ሰኞ፣ ሰኔ 18 2010

የ«ህወሓት» ማዕከላዊ ኮሚቴ ከውሳኔው ይልቅ በተለይ የተቃወመው የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ውዝግብን ለማስወገድ የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በተስማማችበት መሠረት ገቢራዊ እንዲሆን መወሰኑ ለሕዝብ ይፋ የተደረገበት መንገድ አንዱ ነዉ። በብዙዎች ዘንድም መነጋገርያ የሆነዉ ይኸዉ ጉዳይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/30ATv
Infografik Karte Gebietskonflikt Eritrea / Äthiopien EN

የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ግንኙነት፤ የኢህአዴግ ዉሳኔና ህወሓት

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈዉ ረቡዕ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለቱን አገሮች ውዝግብ ለማስወገድ ያሳለፈዉን ዉሳኔ እንደሚደግፍ ፍንጭ ሰጥተዋል። ጉዳዩን የሚያጠና የልዑካን ቡድንም ወደ አዲስ አበባ ለመላክ አቅደዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድም የፕሬዚዳንት ኢሳያስን መግለጫ አወድሰዉታል። የሁለቱ ሃገራት መንግሥታት ሰሞኑን ያሳዩት መቀራረብ 20 ዓመታት ያስቆጠረዉን ጦርነትና ውዝግብ ለማስወገድ ይጠቅማል የሚል ተስፋን አሳድሮአል።  ይሁንና የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ «ህወሓት» ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፈዉ ሰኔ 6 ቀን ያወጣዉ መግለጫ በገዢዉ ፓርቲ መካከል ልዩነት እንዳለ ጠቋሚ ነዉ የሚሉ አሉ። የ«ህወሓት» ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ ከዚያ በፊት ተሰብስቦ የነበረዉ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተገቢው መንገድ ዉይይት ተደርጎባቸዉ ይፋ የተደረገ አይደለም በማለት ተቃዉሞ አሰምቷል። የ«ህወሓት» ማዕከላዊ ኮሚቴ ከውሳኔው ይልቅ በተለይ የተቃወመው የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ውዝግብን ለማስወገድ የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በተስማማችበት መሠረት ገቢራዊ እንዲሆን መወሰኑ ለሕዝብ ይፋ የተደረገበት መንገድ አንዱ ነዉ። በብዙዎች ዘንድም መነጋገርያ የሆነዉ ይኸዉ ጉዳይ ነዉ። ከዚህ በመነሳትም ከሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰማዉ ተቃዉሞ በዶክተር ዐብይ የሚመራዉ መንግሥት የጀመራቸዉን የታሃድሶ ለዉጦች ለማደናቀፍ የሚደረግ ሙከራ ነዉ የሚሉ አሉ። ሌሎች ደግሞ የኢህአዴግ መሪዎች የጋራ አቋም መያዝ እንደተሳናቸው ያመላክታል ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአልጀርስን ስምምነት በተመለከተ ስለተነሳዉ ተቃዉሞ በያዝነዉ ነው ሳምንት ለም/ቤቱ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል። በማብራርያቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነቱንና የድንበር ኮሚሽኑን ዉሳኔ የተቀበለው ከ 16 ዓመት በፊት መሆኑን አመልክተዋል። ይህ ደግሞ ለህወሓት እንግዳ ሊሆን አይገባም የሚሉ አሉ። ስለዚህ የተቃውሞው ምንጭ የአልጀርሱ ስምምነት ሳይሆን ሌሎች ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ የሚለዉን ግምት ይበልጥ እያጎላዉ መጥቶአል። የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ግንኙነት የኢህአዴግ ዉሳኔና የህወሓት ተቃዉሞ መወያያ ርዕሳችን ነዉ። በዉይይቱ እንዲሳተፉልን የጋበዝናቸዉ፤ አቶ ሃሌሉያ ሉሌ የፖለቲካ ተንታኝ፤ አቶ አብርሃም ገብረአረጋዊ ጋዜጠኛ እና የቀድሞ የህወሓት አባል እንዲሁም በኪል-ብሪታንያ ዩኒቨርስቲ የሕግ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸዉ። 

Karte Ethiopia und Eritrea ENG


ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ