1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወታደራዊ ሹም ሽር በሳዑዲ

ረቡዕ፣ የካቲት 21 2010

ሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የጦር አዛዦቿን ባልተለመደ መልኩ ቀያየረች፡፡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፣ የአየር ኃይል ጠቅላይ አዛዥም ሆነ የምድር ጦር አዛዥ የነበሩት ከፍተኛ ጀነራሎች ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ የሲቪል እና የሀገር አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችም ሹም ሽር ተደርጓል፡፡

https://p.dw.com/p/2tTaT
Russland Mohammed bin Salman
ምስል picture-alliance/dpa/AP Photo/Pool/P. Golovkin

የሹምሽሩ መንስኤ የተለያዩ መላምቶችን አስከትሏል

 በተለይ በከፍተኛ የጦር አመራሮቹ ሹም ሽር በተመለከተ የተለያዩ  አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ መውጫ ያጣውን  የየመን ጦርነት በተለየ ዘይቤ ለማስተናገድ ነው የሚሉ መላ ምቶች ባንድ በኩል ፤ ለወጣቱ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን ቀጣይ ስልጣን መንገድ መጥረግ የሚሉት በሌላ በኩል አስተያየቶቹን ይመራሉ፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት በእንግሊዝ ጉብኝት ለማድረግ መርሐ ግብር የያዙት አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን በየመን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሳዑዲ መራሹ ወታደራዊ ኃይል በሚያደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ተደጋጋሚ ነቀፌታ ለሚያደርሱባቸው የአሜሪካ እና የአውሮጳ ባለስልጣናት ለውጥ ማድረጋቸውን ለመግለጽ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተንታኞች ያብራራሉ፡፡ ከሪያድ ስለሺ ሽብሩ ተጨማሪ ዘገባ አለው

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ