1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለመጠየቅ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኃላፊ ጋር

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2011

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ መሥሪያ ቤታቸው «ወንጀል በተፈፀመባቸዉ አካባቢዎች ሁሉ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የድርጊቱ ተሳታፊ ወይም ተጠርጣሪ አካላትን ጉዳይ እየመረመረ ለህግ የማቅረብ ሂደት ላይ እንደሚገኝ» ለDW ገለፁ።

https://p.dw.com/p/39Xgd
Äthiopien Polizei
ምስል imago/Xinhua

MM T/ Interview with Zenabu Tunu, Spox at Attorney General - MP3-Stereo

ቀደም ሲል በጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሚመራ ከፌዴራል ፖሊስና ከሌሎች ጸጥታ አካላት የተወጣጣ ግብረ-ኃይል በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የተፈጠረዉን ግጭት ለመመርመር መሰማራቱ ተነግሯል። ግብረ ኃይሉ በግጭቱ ላይ በቀጥታ የተሳተፉ ወይም ከጀርባ ሆነው ያቀነባበሩትን ለይቶ ለፍትሕ እንዲቀርቡ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊዉ አክለው ገልፀዋል። መርጋ ዮናስ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑን ዛሬ እኩለ ቀን ላይ በአጭሩ አነጋግሯጠዋል። 

ሙሉ ቀለመጠየቁን ለመከታተል አዉዲዮዉን ይጫኑ። 

መርጋ ዮናስ

ሼዋዬ ለገሰ