1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከህወሓት እና ከብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ምን ይጠበቃል?

ዓርብ፣ መስከረም 18 2011

12 ኛዉ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በኃላ ባህርዳር ላይ ተጀምሮአል።ትናንት በመቐለ ከተማ በይፋ የተጀመረዉ 13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ/ህወሓት/  ድርጅታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ የተጀመረዉን የለዉጥ ሂደት ለማስቀጠል በሚያስችል ሁኔታ እንደሚወያይ ተገለጿል።

https://p.dw.com/p/35bG5
Äthiopien ANDM Kongress in Baherdar
ምስል M. Kebede

12 ኛዉ የብአዴን እና 13ኛው የህወሓት ጉባኤ

ትናንት በመቐለ ከተማ በይፋ የተጀመረዉ 13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ/ህወሓት/  ድርጅታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ የተጀመረዉን የለዉጥ ሂደት ለማስቀጠል በሚያስችል ሁኔታ እንደሚወያይ ተገለፀ። በሌላ በኩል ባህርዳር ላይ ዛሬ ከቀትር በኋላ ጉባኤዉን የጀመረዉ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸዉን ስራዎች መገምገምን ጨምሮ በሦስት አብይ ነጥቦች ላይ እንደሚወያይ ተመልክቶአል።        

Äthiopien TPLF Kongress in Mekele
ምስል A. Gebereselasse

12 ኛዉ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በኃላ ባህርዳር ላይ ተጀምሮአል። በጉባኤዉ የድርጅቱ አባላት የመረጥዋቸዉ  1200 ተወካዮች፤ ተጋባዥ እንግዶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 2100 ሰዎች በጉባኤዉ እንደሚካፈሉ የድርጅቱ ማዕከላዊ ምክር ቤት ጽ/ ቤት የገጠር ፖለቲካ እና አደረጃጀትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ለ «DW» ተናግረዋል። ብአዴን ስሙን እና አርማዉን በተመለከተ የሚሻሽለዉ አንቀጽ ሰፋ ያለ የጉባኤዉን ሰዓትም ይወስዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና በጉባኤዉ አማራጭ ስምና አማራጭ አርማ ተዘጋጅቶ መቅረቡን አቶ ምግባሩ ከበረ ተናግረዋል።  

ድርጅቱ እስካሁን ያገዳቸዉ አቶ በረከት ስምኦን እና ታደሰ ካሳ ን በተመለከተ ዉሳኔ ይሰጣልም ተብሎአል። ነገ ማታ አልያም ቅዳሜ ጠዋት እንደሚጠናቀቅ የተነገረዉ  በ 13 ኛዉ የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ ከሰላምና ልማት እንቅስቃሴዉ በተጨማሪ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓትና መንግስትን ለማፍረስ የሚጣጣሩ ኃይሎችን እንደሚታገል የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤዉ መክፈቻ ተናግረዋል። በድርጅቱ የተጀመረውን የተሃድሶ ጉዞ ከግብ ለማድረስ የክልሉ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆምም ጠይቀዋል። የህወሓት መስራች የነበሩት አቶ አስገደ ገብረስላሴ በበኩላቸዉ ፓርቲዉ ከጉባኤዉ በኃላ ፋይዳ ማምጣቱን ይጠራጠራሉ።

Äthiopien TPLF Kongress in Mekele
ምስል A. Gebereselasse

የአማርን ጨምሮ የኦዴፓ ድህዴን አጋር ፓርቲዎች በጉባኤዉ ንግግር አድርገዋል ፤ እንደዉም ፓርቲዉ ለመጀመርያ ጊዜ የተቃሚ ፓርቲ አባላትን አሳትፎአል በጉባኤዉ መክፈቻ ንግግር አሰምተዋል።  በጉባኤ ብዙ ሴቶችን ያካተተ ወጣት አባላት በፓርቲዉ እንደሚያካት ፓርቲዉ ገልፆአል።  ለአምስት ቀናት ጉባኤ የተቀመጠዉ ህወሓት ከጋራ ምክር ቤት አባላት በተጨማሪ ከአገር ዉስጥ አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በተጨማሪ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ እና የደቡብ አፍሪቃ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ተወካዮች በጉባኤዉ  መክፈቻ መገኘታቸዉ አጋርነታቸዉን ማሳየታቸዉ ተመልክቶአል። 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ