1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦነግ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተስማማ

Merga Yonas Bula
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 1 2010

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ የተመራው እና ትናንት ወደ አሥመራ፣ ኤርትራ የተጓዘው የልዑካን ቡድን ዛሬ ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር፣ ኦነግ መሪ ዳዉድ ኢብሳ ጋር ተገናኝቶ ውይይት አካሄደ።

https://p.dw.com/p/32lW3
 Logo Oromo Liberation Front

OLF agreed to return to Ethiopia - MP3-Stereo

በዚሁ አራት ሰዓት በቆየው ውይይት ላይ ኦነግ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በአገሪቱና በኦሮሚያ ክልል ጉዳዮች ላይ በሰላማዊ መንገድ ለመስራት እንደተስማማ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ለዶይቼቬሌ ተናግረዋል። አቶ ቶሌራ፣ «ኦነግ ወደ አገር ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ እንዲሰራ ተስማምተናል። ከዚህ በኋላ በኦሮሞና በአገሪቱ ጉዳዮች ላይ በሰላማዊ መንገድ ተባብሮ ይሰራል። በስምምነቱ መሰረት፣  ኦነግ ካሁን በኋላ በሀገሪቱ በነፃ፣ ሳይፈራ መንቀሳቀስ ይችላል።»

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ኤርትራን በጎበኙበት ጊዜ  ከኦነግ ልዑካን ቡድን ጋር ሐምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም ተገናኝቶ መወያየታቸዉ ይታወሳል። ግንባሩም ጊዜሻዊ የቱክስ ማቆም ማወጁም ይታወሳል። ይሁን እንጅ ኦነግ እሄን ተከትሎ ከጥቅት ቀናት በዋላ ባወጣዉ መግላጫዉ የኢትዮጵያ መንግስት የግንባሩ ጦር ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን የመከላክያ ሰራዊት አሰማርተዋል በምል ክስ ድርድሩ ለግዜዉ እንድቋረጥና የቱክስ ማቆም አዋጁን ማንሳቱ ተዘግበዋል።

ዛሬ በተደረገዉ ስምምነት ተከትሎ ኦነግና የኢትዮጵያ መንግስት የተኩስ አቁም ደንብ መድረሳቸውንም ቃል አቀባዩ አቶ ቶሌራ አዳባ ገልጸዋል። አቶ ቶሌራ፣ «አንድ ሌላ የተስማማንበት ጉዳይ ደግሞ ከዚህ በኋላ በኦነግ ስም ምንም አይነት የጦር ርምጃ እንዳይወሰድ ነዉ። ከዛሬ በኋላ በመካከላችን ሲካሄድ የነበረዉ የኃይል ርምጃም በይፋ እንዲቆም ተስማምተናል። የኦነግ ሰራዊትን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ወደፊት በጥልቀት እንወያይበታለን።  አሁንም ግን የኦነግ ሰራዊት እንደ ኦነግ ሰራዊት ባለበት ይቆያል።»

Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Deutsch

ዉይይቱ ኦነግን ሀገር ውስጥ ገብቶ በሰላም መንቀሳቀስ እንዲችል ያደርጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ የተናገሩት የአሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በክልሉ ምዕራባዊ፣ ምሥራቃዊ እና ደቡባዊ አካባቢዎች በኦነግ ስም ሲካሄድ የነበረ ግጭት ካሁን በኋላ እንደማይቀጥል እምነታቸውን ገልጸዋል። የድርድሩን ሂደት በተመለከተ በ«አዎንታዊ ኃይል ወደፊት እየሄደን» ነዉ የሚሉት ዶክተር ነገሪ ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን በሰላማዊ መንገድ ይፈታሉም ብለዋል።

የተጀመረዉን ድርድር ለማስቀጠል  በመጀመሪያ አንድ የኦነግ የልዑካን ቡድን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዝ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አስታውቀዋል። አቶ ቶሌራ፣«የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት አንድ የኦነግ የልዑካን ቡድን በሁለትና ሶስት ቀን ዉስጥ ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል።  በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉ የኦነግ አባላት ግን  ሁኔታዉ ከተመቻቸ በኋላ፣ ማለትም፣  ከሁለቱም በኩል የሚውጣጣ አንድ ኮሚቴ ከተቋቋመ በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱት።»

በኦነግ እና በመንግሥት መካከል የመጀመሪያዉ ድርድር ከተሰናከለ ወደህ የግንባሩ ሰራዊትና የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት በምዕራብ ኦሮሚያ ስጋጩ እንደነበረ አቶ ቶሌራ ገልፀዋል። መቀመጫዉን ኤርትራ ያደረገዉ ኦነግ ኢ/ኤ/አ ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ ሠራዊቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ