1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እኔም ተደምሬያለሁ» -ድምጻዊው

እሑድ፣ ሰኔ 24 2010

«እኔ በዚህ ሙዚቃ ከተደመርኩ ቆየሁ። አሁን ደግሞ ደስ በሚል መልኩ ዳግም ተደምሬያለሁ፤ ተመሳሳይ ታሪካዊና የኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚሰብኩ አዳዲስ ሙዚቃዎቼን ይዤ በቅርቡ ሃገሪ እመለሳለሁ ብሎናል፤ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን በማድነቅ በማክበር።

https://p.dw.com/p/30ZKf
Gizachew Tekelmariam äthiopischer Musiker
ምስል Privat

«አሁንማ ሁላችንም ተሰብስበን ወደ ሃገራችን»

በየነ ወንድም አገኘሁ አልያም በፈረስ ስማቸው «አባ ሰብስብ» በመባል የሚታወቁት ኢትዮጵያዊዉ አርበኛ በማኅበረሰቡ ዘንድ «ሊጋባዉ በየነ» በሚል ስማቸዉ በተለይ ይታወቃሉ ። የክራርና የመስንቆ አባቱ ድምጻዊው ግዛቸው ተክለማርያም «ኸረ ምነው… ምነው! ኸረ ምነው ምነ!፤ ከራስ በላይ ወዶሽ ሊጋባዉ በየነ» ሲል ባወጣዉ ዜማ ታሪካቸዉን በመሰንቆ አዋዝቶ ለአድማጭ ጆሮ ካደረሰዉ ስድስት ወር ሊሆነዉ ነዉ። ድምጻዊ ግዛቸዉ እንደሚለዉ «እኔ በዚህ ሙዚቃ ከተደመርኩ ቆየሁ። አሁን ደግሞ ደስ በሚል መልኩ ተደምሬያለሁ፤ ተመሳሳይ ታሪካዊና የኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚሰብኩ አዳዲስ ሙዚቃዎቼን ይዤ በቅርቡ ሃገሪ እመለሳለሁ ብሎናል፤ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን በማድነቅ በማክበር። «እንደኮራ ሄደ እንደተጀነነ፤ ጠጅ ጠጣ ሲሉት ዉኃ እየለመነ፤ የጎንደር ባላት ሊጋባዉ በየነ»

Gizachew Tekelmariam äthiopischer Musiker
ምስል Privat

«ሊጋባዉ በየነ» በሚል ታሪካቸዉ የሚታወቁት በየነ ወንድም አገኘሁ፤ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን በደጅ አጋፋሪነት፤ በልጅ እያሱ ዘመን በሊጋባነት፤ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱና በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ዘመን ደግሞ፤ በደጃዝማችነት የሚታወቁ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ጀግና በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች አገረ ገዢ ሆነዉ አገልግለዋል። በዘመናቸዉ መንግሥትን በመሞገታቸዉ፤ ብዙ ጊዜ ታስረዋል። ለአሰረኝ መንግሥት ስልጣን ይዤ አጎብድጄ አልኖርም ብለዉ የተሰጣቸዉን ስልጣን አልተቀበሉም። ኢትዮጵያን ጠላት ሲወር ግን ከነበሩበት እስር ቤት ለንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱና በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ለሚመራዉ መንግሥት ጠላትን መዉጋት እንደሚፈልጉ ጽፈዉ ፤ ጠላትን ሲመክቱ ወድቀዋል። በዚህም አርበኛ በየነ ወንድም አገኘሁ «ሊጋባዉ በየነ» ለኢትዮጵያ በከፈሉት መስዕዋትነት ታሪክ ዘላለም ይዘክራቸዋል። 

Gizachew Tekelmariam äthiopischer Musiker
ምስል Privat

በቅርቡ ድምጻዊ ግዛቸዉ ተክለማርያም ለአድማጭ ጆሮ ያደረሰዉ የሊጋባዉ በየነን መንፈስ የሚያስቃኝ ሙዚቃ ለሃገር አንድነት የቆሙ ስማቸዉ የማይታወቅ ኢትዮጵያዉያንን ሁሉ የሚወክል በመሆኑ ብዙዎች ዘንድ እንደተወደደ ነግሮናል። በየነ ወንድም አገኘሁ አልያም «ሊጋባዉ በየነ» ለኢትዮጵያ በከፈሉትን የመስዕዋትነት ታሪክ ሲያወሳቸዉ ይኖራል።

ሙሉ ቃለምልልስ የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ