1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እነ እስክንድር እንደታሰሩ ነው

ሰኞ፣ መጋቢት 17 2010

ጎተራ በሚገኘው ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት እነዚሁ ሰዎች ለፖሊስ ቃላችንን አንሰጥም ማለታቸውን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል።12 ቱ ሰዎች የታሰሩት ፣በቅርቡ ከእስር ለተለቀቁ ሰዎች ትናንት በተዘጋጀ የምስጋና መርሃ ግብር ከተገኙበት ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መኖሪያ ቤት ነው።

https://p.dw.com/p/2v1aE
Äthiopien Eskindr Nega und Andualem Arage
ምስል Serkalem Fassil

ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞቹ እንደታሰሩ ነው

በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬም እንደታሰሩ ነው። ጎተራ በሚገኘው ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት እነዚሁ ሰዎች ለፖሊስ ቃላችንን አንሰጥም ማለታቸውን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል።  ከጋዜጠኞቹ እና ፖለቲከኞቹ በተጨማሪ አክቲቪስት እና ጦማሪዎችም ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል። ዛሬ ሰዎቹ የታሰሩበት ቦታ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ