1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስከ ዛሬ ማምሻ በይቅርታ የተፈታ የለም።

ዓርብ፣ የካቲት 2 2010

በተለይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌ ዛሬ እንዲፈርሙ ተሰጣቸው የተባለ ፎርም ይዘት ውዝግብ አስነስቶ መግባባት ላይ አለመድረሳቸውን ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል።

https://p.dw.com/p/2sQmB
Äthiopien Eskindr Nega und Andualem Arage
ምስል Serkalem Fassil

እስከ ዛሬ ማምሻ በይቅርታ የተፈታ እንደሌለ ዘጋቢያችን ገልጾልናል።

በይቅርታ እንዲፈቱ ተወስኖላቸዋል ከተባሉት ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች መካከል እስከ ዛሬ ማምሻ ድረስ የተፈታ አለመኖሩን ወደ ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የተጓዘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ገልጾልናል። መንግሥት እስረኞች እንዲፈቱ ወስኗል ከተባለ በኋላ ከዛሬ ጠዋት አንስቶ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነዉ።  በተለይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌ ዛሬ እንዲፈርሙ ተሰጣቸው የተባለ ፎርም ይዘት ውዝግብ አስነስቶ  መግባባት ላይ አለመድረሳቸው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል። አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እስረኞችን በመፍታት ሂደት ተነሱ በተባሉ ውዝግቦች ላይ አስተያየት እየሰጡ ነው። ይህን እና ከእስረኞች መለቀቅ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ወደ ቅሊንጦ ሄዶ የነበረውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን በስልክ አነጋግረነዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ