1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል ስደተኞችን ለመመለስ በዝግጅት ላይ ናት

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ጥር 24 2010

የእስራኤል መንግስት በሺህዎች የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ስደተኞችን ወደ አገራቸዉ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ነው። የእስራኤል እቅድ በአለማቀፉ ማህበረሰብ እየተተቸ ነው።

https://p.dw.com/p/2ru8J
Asylsuchende protestieren gegen israelische Regierung
ምስል picture-alliance/dpa

The Sage of Refugee Deportation in Israel - MP3-Stereo

የእስራኤል እቅድ በሀገር ዉስጥ ለዘብተኛ ከሆነው የማህበረሰቡ ክፍል እንዲሁም ከተባባሪያቸው አይሁድ አሜሪካውያን በኩል ያልተጠበቀ ትችት እንደገጠመው አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። የነሱም መከራከርያ ነጥብ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአይሁዶች ላይ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ በኋላ የተመሰረተችዉ እስራኤል ተገን ለሚያሻቸው ስደተኞች ጀርባዋን መስጠት የለባትም የሚል ነዉ። በአሁኑ ጊዜ ስደተኞቹ ይዉጡ አይዉጡ በሚለዉ ጉዳይ ላይ የእስኤራል ማህበረሰብ መከፋፈሉን የዶይቼ ቬሌ የእስራኤል ወኪል አቶ ዜናን መኮንን ይናገራል።

እስራኤል ዉስጥ ከሚኖሩት ስደተኞች ከኤርትራና ከሱዳን የመጡት በዚህ እቅድ እንደሚጠቃለሉ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ለስደተኞች መብት የሚሟገተ Hotline for Refugees and Migrants የተሰኘዉ ቡድን የእስራኤል መንግሥት ለእያንዳዳቸዉ 5000 ዶላር በመስጠት 40ሽ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንደሚልክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የቡድኑ ቃለአቀባይ ድሮር ሳዶት ተገን ጠያቂ የሱዳንና የእርትራ ስደተኞችን የእስራኤል መንግስት ስደተኞች ብሎ ከመጥራት ሰርጎ-ገቦች እንደሚላቸው ለዶይቼ ቬሌ ገልፀዋል። ስደተኞች አይዉጡ ሲሉ የሚሟገቱ የህብረተሰብ ክፍሎች አቋም ተስፋ ሰጭ መሆኑን የተናገሩት ድሮር ሳዶት ከህብረተሰቡ አመዛኙ ስደተኞቹ መቆየታቸው እንደሚደግፍ ነው የገለጹት።ድሮር ሳዶት: «አዎ በማህበረሰቡ ዉስጥ በዝህ ጉዳይ ላይ ክፍፍሎች አሉ። ግን ስደተኞቹ ከእስራኤል እንደወጡ በዋነኛነት ኢየነዛ ያለዉ የኢስራኤል መንግስት እንጅ ማህበረሰቡ አይደለም። ስደተኞቹ እዝህ አጋር ዉስጥ ከአስርት-አመታት በላይ ኖሮዋል ግን መንግስት በተቻለዉ መጠን እንደ ወንጀለኞች ይቆጥራቸዋል። በእስራኤል ዉስጥ ያለዉ አብዛኛዉ ማህበረሰብ እዉነት ለመናገር እነዝህ ስድተኞች እንድሄዱ አይፈልጉም።»

Flüchtlingslager Holot für afrikanische Asylsuchende in Israel
ምስል Getty Images

የኤርትራና የሱዳን ስደተኞች እንዲወጡ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ሌሎች ስደተኞች ወደ እስራኤል ለመግባት እንደሚሞክሩ ዜናነህ ያስረዳል።

ስደተኞቹ ባለፈው ሳምንት  የእስራኤል መንግሥትን ውሳኔ በመቃወም ባካሂዱት ሰላማዊ ሰልፍ  ሰንሰለት አንገታቸዉ ላይ በማሰር፣  አፋቸዉ ላይ ፕላስተር በመለጠፍ ተቃዉሞቸዉን ገልጸዋል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ