ውይይቱ ኢትዮጵያ ገጥመዋታል በተባሉ ችግሮች ላይ ተነጋግሯል።
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2010ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል? ተቃዋሚው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ በሳምንቱ መገባደጃ ባካሔደው የውይይት መድረክ የተሳተፉ አንድ ግለሰብ ይኸ ሥጋት አድሮባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በሊቢያ እና በሶማሊያ መንገድ ላለመጓዙ ማንም የሚያውቅ የለም ሲሉ ተደምጠዋል። "ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?" በሚል መሪ ቃል በተካሔደው ውይይት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እና ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጨምሮ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዜጎች ታድመውታል። ውይይቱ ኢትዮጵያ ገጥመዋታል በተባሉ ችግሮች ላይ ተነጋግሯል። ተመሳሳይ ውይይቶች በወርኃ ታኅሳስ በተከታታይ እንደሚደረጉ ፓርቲው አስታውቋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ