1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ፍኖተ ካርታ ለትምህርት ጥራት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2011

የኢትዮጵያ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጥልቅ ጥናት ተደርጎበት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን አካትቶ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡ የቬትናምንና ማሌዥያን እንዲሁም የሌሎችን ሃገሮች ልምድ በማካተት የተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታው ለሚቀጥሉት 15 አመታት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/3A3Ng
Doktorhut auf einem Bücherstapel
ምስል picture.alliance/blickwinkel/BilderBox/McPHOTO

«የሌሎች ሃገራትን የሥራ ልምድ አካትቶ የተዘጋጀ ነው»

 የትምህርት ሚኒስትሩ ሮክተር ጥላየ ጌቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ፍኖተ ካርታው ብዙ አከራራካሪ ጉዳዮች ተነስተውበታል፡፡ በቀጣዮቹ 1 5አመታት  ፍኖተ ካርታው ሊያመጣው የሚፈለገውን ግብም የመለየት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡ዋነኛው የዚህ ፍኖተ ካርታ አስፈጻሚ ትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን አሁን ያለው አጠቃላይ የሚኒስቴሩ እና የደረጃው መዋቅር ይህንን ፍኖተ ካርታ ለማስተግበር የማያስችል በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሁለት ተከፍሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተተዋቅሯል፡፡ የትምህርት ፍኖተ ካርተታው ከ እስከ ዛሬው አካሄድ በተለየ ከመጽደቁ በፊት መላው ህዝብ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በስፋት ይወያይበታል ፡፡ የሃገሪቱን ሁለንተናዊ ሁኔታ የሚወስን እንደመሆኑ መጠን ከ 7ኛ ክፍል ጀምሮ ካሉ ተማሪዎች እስከ በውጭው አለም የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ሃሳብና አስተያየት እንዲሰጡበት ይደረጋል ፡ የደርግ ባለስልጣን የነበሩት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴም ጽሁፍ በመስጠት ተካፍለውበታል ፡፡ይህ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የትምህርት ቤት መግቢያን ከ 7 አመት ወደ 6 ማድረግ የሚል ሃሳብ መያዙ ተነግሯል፡፡በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሚገባ ተማሪም መጀመርያውን አንድ አመት ሙሉ ሃገሪቱን ታሪክ ፡ ባህልና መልክአምድር በማጥናትና በመማር ግብረገብነትን ያዳበረ ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅን እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል፡፡በአጠቃላይ የትምህርት ስርአቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል ተባለለት ይህ ፍኖተ ካርታ ማናኛውም ተማሪ ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ፡ ከአማርኛ እና እንግሊዝኛ በተጨማሪ ሌ አንድ የሃገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማር ያደርጋል፡፡ ፍኖተ ካርታው 700 ገፅ ያለው የጥናት ውጤት ስለመያዙም ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ተጨማሪ ዘገባ አለው።

ሰሎሞን ሙጬ

 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ