1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶፊያ እና ሉሲ ተዋወቁ

ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2010

ሶፊያ ለትርኢት የቀረበችዉም  ከሉሲ ጎን ነዉ።በ1992 «ሠላም» የተሰኘዉን ቅሬተ አፅም ያገኙት ኢትዮጵያዊዉ እንትሮፖሎጂስት ዘረሰናይ ዓለም ሰገድ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የሰዉ ልጅ መገኛ የሆነችዉ ኢትዮጵያ፤የዘመናዩ ቴክኖሎጂ ዉጤት የሆነችዉን ሶፊያን ማስተናገዷ የሚደነቅ ነዉ።

https://p.dw.com/p/30lYv
Die Rolle von Kunst in der Politik und der Gesellschaft
ምስል Fitsum Arega

ሶፊያ የተባለችዉ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ሮቦት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘጋጀዉ አዉደ ትርኢት ለሕዝብ ታየች። አማርኛ ቋንቋ እንድትናገር ኢትዮጵያዉን አዋቂዎች መናገሪያ የገጠሙላት ሮቦት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተገኘችዉ ከጥንታዊቷ ሰዉ ድንቅነሽ ወይም ሉሲ ቅሬተ-አፅም ጋር ተዋዉቃለችም።ሶፊያ ለትርኢት የቀረበችዉም  ከሉሲ ጎን ነዉ።በ1992 «ሠላም» የተሰኘዉን ቅሬተ አፅም ያገኙት ኢትዮጵያዊዉ እንትሮፖሎጂስት ዘረሰናይ ዓለም ሰገድ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የሰዉ ልጅ መገኛ የሆነችዉ ኢትዮጵያ፤የዘመናዩ ቴክኖሎጂ ዉጤት የሆነችዉን ሶፊያን ማስተናገዷ የሚደነቅ ነዉ።ሶፊያ አዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ከመቅረቧ በፊት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ጋር ተገናኝታለች።ሶፊያ የተሰራችዉ ሆንግ ኮንግ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ