ታማኝ በየነን ለመቀበል ዝግጅቱ ተጠናቋል
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 22 2010አርቲስቶቹን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየረ ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ መለስዓለም እንዲሁም የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ አቀባበል እድርገዉላቸዋል። በቀጣይ ለ 27 ዓመታት በዩናይትስ ስቴትስ ስደት ላይ የነበረችዉና ዛሬ ወደ ሃገርዋ የገባችዉ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ በብሔራዊ ትያትር ደማቅ አቀባበል ሥነ-ስርዓት ተደርጎላታል። ብሔራዊ ትያትር ከተካሄደዉ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት በኃላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን አርቲስት ዓለምፀሓይ ወዳጆ፤ አርቲስት አበበ በለው እና አርቲስት ተክሌ ደስታን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የጥበብ ሰው የጎደለውን የሚተች ብቻ ሳይሆን የጎደለውን የሚሞላ ጭምር ነው ሲሉ መናገራቸዉ ተመልክቶአል። ለዓመታት በአዉስትራልያ ስደት ላይ የነበዉ አርቲስት ተስፋዬ ገብረሃናም ዛሬ አዲስ አበባ ከገቡት አርቲስቶች መካከል አንዱ ነዉ። በሌላ በኩል የፊታችን ቅዳሜ ማለዳ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ በጉጉት ስለሚጠበቀዉ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አቀባበል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቶ ነበር። ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ዝርዝሩን ተከታትሎአል።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ