አሳሳቢዉ የእስረኞች የስቃይ አያያዝ
እሑድ፣ ኅዳር 24 2010ማስታወቂያ
ይህን ሕግ ተቀብለዉ ከፈረሙ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በይፋ የሚሰማዉ የሀገሪቱ የአስረኞች አያያዝ አሳሳቢ እና አነጋጋሪ ሆኗል። እስር ቤት ዉስጥ ስቃት የሚፈፀምባቸዉ፤ በአያያዛቸዉ ምክንያትም ለሕልፈተ ሕይወት ብሎም ለአካል ጉዳት እና ሕመም የተዳረጉ የመኖራቸዉ አቤቱታ የፍርድ ቤት ችሎቶች በየጊዜዉ የሚሰሙት መሆኑም እየተዘገበ ነዉ። አቤቱታ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመሆኑም ሌላዉ ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ሆኗል። ዶቼ ቬለ አሳሳቢዉን የእስረኞች የስቃይ አያያዝ ሁኔታ የቃኘ ዉይይት አካሂዷል።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ