1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አመፅና ግጭት በዩናይትድ ስቴትስ

ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2009

በዩናይትድ ስቴትሷ ቨርጂኒያ ግዛት በሳምንቱ መጨረሻ የታየዉ ደማ አፋሳሽ አመፅ የሌሎች ሃገራትን መንግስታት ትኩረት ስቧል። በነጭ ብሔርተኞች እና ኒዮ ናዚዎች የተዘጋጀዉ የነጭ ቀኝ አክራሪዎች ሰልፍ፤ የእነሱን አቋም በሚጻረሩ የሀገሪቱ ዜጎች ተቃዉሞ ሲገጥመዉ የተቀሰቀሰዉ ግጭት ሕይወት እስከመቅጠፍ ዘልቋል።

https://p.dw.com/p/2iD5J
USA Virginia - Ausschreitungen nach Demonstrationen
ምስል Getty Images/C. Somodevilla

 የተጎዱትም ቁጥራቸዉ በርከት ያለ ነዉ። ሀገሪቱን አንድ ለማድረግ እንደሚሠሩ የሚናገሩት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ነጭ የቀኝ ፅንፈኞቹን ነጥለዉ  ባለማዉገዛቸዉ እየተተቹ ነዉ። አካሄዱ ያሰጋቸዉ ወገኖች በቀጣይ ምን ሊከሰት ይችላል በሚል እየጠበቁ ቢሆንም ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ ሸዋዬ ለገሠ በስልክ ያነጋገረችዉ የዋሽንግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ግን መብረዱን ገልጾልናል። መክብብ አሁን ያለዉን ሁኔታ በመግለፅ ይጀምራል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ