በጸረ-ሽብር ሕጉ የተከሰሱ ይፈቱ ይሆን?
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 27 2010ማስታወቂያ
ተቺዎቹን እና ተቃዋሚዎቹን ያስራል፤ ያሳድዳል እየተባለ የሚወቀሰው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እስረኞችን ሊፈታ መዘጋጀቱን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንዳሉት የሚፈቱት «በፈጸሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ በአቃቤ-ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው እና ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ሆነ ግለሰቦች» ናቸው።
«የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሲባል» ከእስር የሚፈቱት ግለሰቦች ማንነትም ሆነ ብዛት እስካሁን በይፋ አልተገለጠም። «አንዳንዶቹ ክሳቸውም ተቋርጦ እንደዚሁም ደግሞ የምሕረት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ምሕረት ተደርጎላቸው» ከሚፈቱት መካከል በአወዛጋቢው የጸረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱ ይኖሩ ይሆን? የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የሕግ ባለሙያ ተማም አባቡልጉን አነጋግሯቸዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ