1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎሳ ውዝግብ ሰበብ የቤሮ ማጂ መንገድ መዘጋቱ

ሐሙስ፣ ጥር 9 2011

በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ የቤሮና የማጂ ወረዳዎችን ከዞኑና ከመሀል ሀገር ከተሞች የሚያገናኙ መንገዶች ለወራት ተዘግተው እንደሚገኙ እየተነገረ ይገኛል፡፡  የየወረዳዎቹ ነዋሪዎች ለዲ ደብሊው እንደገለጹት መንገዶቹ የተዘጉት በአካባቢው በሚገኙ ጎሳዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው፡፡ 

https://p.dw.com/p/3Bj5r
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

 በወረዳዎቹ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ሄድ መጣ እያለ በተከሰተው ግጭት አስከአሁን ከስልሳ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለጉዳት መዳረጋቸውን በቤንች ማጂ ዞን የቤሮ ወረዳ መስተዳድር አስታውቋል፡፡  በአሁኑወቅት ግጭቱን ለማስቆምና የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት የጎሳ መሪዎችንና ባህላዊ የአገር ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ የመስተዳድሩ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ 


ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አርያም ተክሌ

ተስፋለም ወልደየስ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ