የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ በጀርመን መወገዙ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2010ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠታቸውን በመቃወም በርሊንን ጨምሮ በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተካሄዱ ተቃዉሞዎች ላይ ፀረ ሴማዊ መፈክሮች መሰማታቸውን የጀርመን መንግሥት አውግዟል። በነዚሁ ሰልፎች የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉንም አሳፋሪ ሲል ኮንኗል። የዶቼቬለ ዋና አዘጋጅ አኒስ ፖል ድርጊቱ ሀሳብን በነጻ ከመግለፅ እና ከዴሞክራሲ መብቶች ጋር የማይገናኝ ነው ስትል በጉዳዩ ላይ በጻፈችው ሀተታ ገልጻለች። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ያቀርበዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ