1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋው ግጭት

ሰኞ፣ ሐምሌ 30 2010

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግርማ ለዶቼቬለ እንደገለጹት ሰዎቹ የሞቱት በግጭት እና ሁከቱ ወቅት በተነሳ እሳት እና እሳቱ ባስነሳው ጭስ ታፍነው ነው። ሃላፊው ከተማዋን ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ ለመመለስ እየተሞከረ መሆኑንም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/32hOm
Äthiopien Dire Dawa City
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የድሬዳዋው ግጭት

በድሬዳዋ አስተዳደር 09 ቀበሌ ትናንት በተፈጠረ ግጭት 10 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግርማ ለዶቼቬለ እንደገለጹት ሰዎቹ የሞቱት በግጭት እና በሁከቱ ወቅት በተነሳ እሳት እና እሳቱ ባስነሳው ጭስ ታፍነው ነው። ሃላፊው ከተማዋን ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ ለመመለስ እየተሞከረ መሆኑንም ገልጸዋል። ድሬዳዋ ዛሬ የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አንድ የዓይን ምስክር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ