1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በየመን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ረሃብ አፋፍ ላይ ነዉ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2011

በዓለማችን በረሃብ አደጋ በአምስተኛ የምግብ ዋስትና ምዕራፍ ደረጃ የምትገኝ ሌላ ተጨማሪ አንድ ሃገር ብቻ ናት ። እሷም ደቡብ ሱዳን ናት። በደቡብ ሱዳን 25 ሺህ ሕዝብ የረሃብ አደጋ ተደቅኖበታል። ስለዚህ በሌላ ቦታ ካለው በአስር እጥፍ የሚልቁ ሰዎች በየመን በአምስተኛው ደረጃ ውስጥ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/39toR
Hungersnot im Jemen
ምስል Reuters/K. Abdullah

20 ሚሊዮን የመናዉያን በምግብ እና የመጠጥ ዉኃ እጦት እየተሰቃዩ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ። ድርጅቱ ትናንት ምሽት ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በየመን ከሚኖረዉ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛዉ በምግብና የመጠጥ ዉኃ ችግር እየተሰቃየ ነዉ ብሏል። በተመድ የአስቸኳይ ርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎዉኮክ ኒዮርክ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት 25 ሺህ የሚሆን የየመን ነዋሪ በረሃብ የመሞት አደጋ ተደቅኖበታል። 
« በየመን 25 ሺህ ሕዝብ አምስተኛ የምግብ ዋስትና ምዕራፍ ደረጃ በተባለዉ በአደገኛ የረሃብ አደጋ ላይ ይገኛል። በምግብ ዋስትና ምዕራፍ ደረጃ መመዘኛ ከ5ኛ ደረጃ ምደባ በላይ የለም። በየመን የምግብ እጦት ቀዉስ ከዚህ ቀደም በዚህ ደረጃ ምንም አይነት ምዝገባን አላደረግንም።» 
ባለፈዉ ሳምንት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች በተገደሉበት በየመኑ የእርስ በርስ ጦርነት የሰብዓዊ ቀዉስ ተከስቶቷል ሲል መግለጫ አዉጥቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት በየመን የሚታየዉ የረሃብ አደጋ በዓለማችን ከፍተኛዉ መሆኑን የተናገሩት በተመድ የአስቸኳይ ርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎዉኮክ ደቡብ ሱዳን ከየመን ለጥቃ የረሃብ አደጋ የሚታይባት ብቸኛዋ ሃገር መሆኗን አስታዉቀዋል።  
«በዓለማችን በረሃብ አደጋ በአምስተኛ የምግብ ዋስትና ምዕራፍ ደረጃ የምትገኝ ሌላ ተጨማሪ አንድ ሃገር ብቻ ናት ። እሷም ደቡብ ሱዳን ናት። በደቡብ ሱዳን 25 ሺህ ሕዝብ የረሃብ አደጋ ተደቅኖበታል። ስለዚህ በሌላ ቦታ ካለው በአስር እጥፍ የሚልቁ ሰዎች በየመን በአምስተኛው ደረጃ ውስጥ ይገኛሉ» 
በየመን የሚታየዉን የረሃብ አደጋ ለመቅረፍ ሊጠባ ወደ ሦስት ሳምንት በቀረዉ በመጭዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት አራት ቢሊዮን ዶላር አስፈላጊ መሆኑ ስለየመን የረሃብ አደጋ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠዉ መግለጫ ላይ ተመልክቶአል።  የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት« WFP» እስከ መጭዉ የካቲት ወር በየመን የሚያድለዉን የምግብ አቅርቦት ከፍ በማድረግ ለ 12 ሚሊዮን የመናዉያን ምግብን እንደሚያድል ማስታወቁ አይዘነጋም። 

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ