1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ያገለገሉ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ

ማክሰኞ፣ መስከረም 22 2011

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገራት በሚገኙ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ያላቸውን ከ90 በላይ ባለሙያዎች ወደ አገር እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ።

https://p.dw.com/p/35tCc
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

ጥሪ የተደረገላቸዉ ከ 4 እስከ 25 ዓመታት የሠሩ ናቸዉ

ጥሪ የተደረገላቸው በአማካኝ ከአራት እስከ 25 ዓመታት በአገልግሎት ዘርፍ ተቋሙን ያገለገሉት ባለሙያዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል።  በጉዳዩ ላይ «DW»  ያነጋገራቸዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንደገለፁት ጥሪ የተደረገላቸው ሠራተኞች በአገልግሎት ዘርፍ ከ 4  እስከ 25 ዓመታት የሠሩ ናቸው።

አቶ መለስ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ 58 ገደማ ሚሲዮኖች አሏት። አሁን ጥሪ የተደረገላቸው ሰራተኞች ከአንድ የተወሰነ ቦታ የተጠሩ እንዳልሆኑ አቶ መለስ ጨምረው ተናግረዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 130 ዲፕሎማቶች ስልጠና ተሰጥቷቸው በተለያዩ ኤምባሲዎች ለሥራ መመደባቸውን አስታውቋል። የተቋሙ አጠናሁት ያለው መዋቅር በጠቅላይ ምኒስትሩ ጸድቆ በቅርቡ የዲፕሎማቶች ዳግም ምደባ እንደሚደረግም አክሏል።

እሸቴ በቀለ  

አዜብ ታደሰ