1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢራን የቀጠለው ተቃውሞ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረ-ሰብ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2010

የዛሬ ዘጠኝ ሳይታሰብ ዓመት ኢራንን የመታው የሕዝብ አመጽ እንደገና ሰሞኑን ብቅ ብሎ ከመዲናይቱ ቴህራን እስከ ገጠር ድንበር ድረስ ሕዝቡን አደባባይ ላይ አሰልፎ የለውጥ ጥያቄን እንደገና አስነስቷል። በሰሜን አፍሪቃ እጎአ በ2011 ዓም የታየው አብዮት እንቅስቃሴም ወደ ኢራን የተሸጋገረ ይመስላል።

https://p.dw.com/p/2qWdR
Deutschland Nürnberg - Exil-Iraner Solidaritätsaktion proteste Iran
ምስል UGC/Siavash Arabkhani

ማሕደረ ዜና፦ ተቃውሞ በኢራን

እስካሁን ድረስ በተቃውሞው 24 ሰዎች መመሞታቸውን፣ በርካቶች መቁሰላቸውን እና ከ450 በላይ ተቃዋሚዎች ታፍሰው እንደታሰሩ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።ለኢራን ችግር መፍትሄ ካልተገኘ ችግሩ ተባብሶ የመካከለኛው ምስራቅን እና የተቀረውንም አከባቢም ያናጋል ተብሎ ተፈርቷል። ሆኖም በኢራን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲወያይ አሜሪካ ሀሳቡን ስታቀርብ ተቃውሞ ቀርቦባታል። ቻይና ውይይቱን “በኢራን የውስጥ ጉዳይ መፈትፈት” ስትል ጠርታዋለች። ተአቅቧቸውን ካሳዩ ሶስት ሀገራት መካከል ደግሞ አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች።

 
ማትያስ ፎን ሀይነ/ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ