በኢሕአዴግ መግለጫ ላይ የተቃዋሚዎች አስተያየት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እራሱ አምኖ በተቀበላቸው ድክመቶቹ ሀገሪቱን መምራት ስለማይችል ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጡ። የሰሞኑ ስብሰባውም ግንባሩን ለማዳን እንጂ ለሕዝቡ የፈየደው ነገር የለምም ብለዋል። እንዲያም ሆኖ ግንባሩ ከኹለት ሳምንት በላይ በዝግ ያከናወነውን ስብሰባ ሲቋጭ ባወጣዉ መግለጫ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን ለማጎልበት ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሳተፍ አማራጭ የለዉም ማለቱን በአዎንታዊ ያጠቀሱም አሉ። የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በማነጋገር የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ