1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳዉድ አረቢያ የአዲስ ከተማ ግንባታ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 16 2010

ሳዑዲ ዓረቢያ በሰሜናዊ ግዛቷ በዓለም በዚህ ዘመን አቻ የማይገኝለት የተባለ ዓለም አቀፍ የቴክኒዮሎጂ ከተማ ልትገነባ ነው ፡፡ አልጋ  ወራሹ መሃመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ ይፋ እንዳደረጉት ለከተማው ግንባታ 5 መቶ ቢሊዮን ዶላር ተመድቧል፡፡

https://p.dw.com/p/2mZAJ
Saudi Arabien Vision 2030 PK Mohammed bin Salman
ምስል /Getty Images/AFP/F. Nureldine

«ዘመናዊ እና ከጽንፈንነት ነፃ ከተማ ትሆናለች፤»

 26.5 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት የሚኖረው  ይህ ከተማ የሚገነባው ለዓለም ሃገራት ሁሉ ቅርብ ነው በተባለው የሰሜናዊ ሳዉዲ ግዛት ግብጽ እና ዮርዳኖስን ተዋስኖ ነው፡፡ ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል ኒዮም ተብሎ ወደ ተሰየመው ታላቅ ከተማ ለመድረስ ፈጀ ከተባለ 8 ሰዓት የአዉሮፕላን ጉዞ ብቻ ነው የሚወስደው፡፡

አልጋ ወራሹ እንዳሉት ሳዑዲ ዓረቢያም ባለፉት 40 ዓመታት ስትከተለው ከኖረችው የወግ አጥባቂ የእስልምና አስተምህሮ ተላቃ ለዘብተኛ የሚባለውን እስልምና ትከተላለች ፡፡ አዲስ የምትመሠረተው የኒዮም ከተማም አሁን ሥራ ላይ ባለው የሳዉዲ ሕግ እና ደንብ ተገዢ አትሆንም ፡፡ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት ከእንግዲህ በሳዑዲ ዓረቢያ ቦታ እንደማይኖራቸውም ነው አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን ያስገነዘቡት፡፡ ስለሺ ሽብሩ ዝርዝር ዘገባ ከሪያድ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ